ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ዘመን ተሻጋሪ የልማት አካሄዶች፡- የ“እረኛዬ” ድራማ ጭብጣዊ ትንታኔ

በዓለም ላይ የሥነ ጽሑፍዘውጎችን የሚመረምሩ ጥናቶች እየተበራከቱ የመጡ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማዎችን ጉዳይ ይዘው የሚነሱቱ ግን ውስን ናቸው። እነዚህንና መሰል ክፍተቶች መነሻ በማድረግ፣ ይህ ጥናት ከእረኛዬ ድራማ የተገኙ ማህበረሰባዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ አካሄዶችን ይዳስሳል፡፡ ከአጠናን ዘዴ አኳያ ጥናቱ የተመሰረተው ፍጹም አይነታዊ (pure qualitative) በሆነ ውስን የጥናት ዘዴ ሲሆን የይዘታዊ ትንተና (content analysis) በመጠቀም በድራማው ውስጥ አሉ የተባሉ አበይት ጭብጦች ላይ ትኩረት ተደርጓል። በአራት ምዕራፎች ከተዋቀሩባቸው 48 የድራማው ክፍሎች ላይ 29 ክፍሎች ታላሚ የናሙና ስልት በመጠቀም ተመርጠዋል። የድራማው እምቅ ጭብጦች እና የተንጸባረቁባቸው መንገዶች በይዘታዊ ትንተና ስልት ተብራርተዋል። በዚህም መሠረት ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ሰባት የልማት አካሄዶች የተለዩ ሲሆን እነዚህም፡- የሀገር በቀል እውቀትን በልማት ማሳለጥ፣ ማህበረሰብን በትምህርት ማብቃት፣ ጎጂ ልማዶችን መዋጋት፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ ለአገራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት፣ ተተኪውን ትውልድ በመልካም ሥነምግባር ማብቃት፣ እና የሀገር ጠላቶችን እና አላማቸውን መለየት ናቸው። በመጨረሻም አገራት የዜጎቻቸውን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን፣ አገራዊ ጥቅምና ክብራቸውን ለማስጠበቅ እና እንደአገር መቀጠል ካለባቸው ከነዚህ የልማት አካሄዶች መማር መተኪያ ሌለው አማራጭ እንደሆነ ከድራማው ትምህርት ሊቀስሙ እንደሚገባ ጥናቱ ጠቁሟል። በመጨረሻም የጥናቱ አንድምታዎችና ሊሄድባቸው ያልቻላቸውን ጉዳዮች በመጠቆም፣ ተጨማሪ ጥናቶች ሊካሄዱ እንደሚገባ ፍላጎቱ ላላቸው ተመራማሪዎች ጥሪው ቀርቧል።

Authors

Publication Details

Journal
National Academic Digital Repository of Ethiopia
Published
2026-02-13
DOI
https://doi.org/10.20372/ajcik.2023.2.2.1455
Primary Topic
Diverse Approaches in Healthcare and Education Studies
Type
article
Field-Weighted Citation Impact
0.00
Controls
|||
ALL TIME
JAN
FEB
MAR
APR
MAY
JUN
JUL
AUG
SEP
OCT
article

ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ዘመን ተሻጋሪ የልማት አካሄዶች፡- የ“እረኛዬ” ድራማ ጭብጣዊ ትንታኔ

አዳነ ኃይሉ ሄሩት
National Academic Digital Repository of Ethiopia
Diverse Approaches in Healthcare and Education Studies
article

ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ዘመን ተሻጋሪ የልማት አካሄዶች፡- የ“እረኛዬ” ድራማ ጭብጣዊ ትንታኔ

አዳነ ኃይሉ ሄሩት
article en

Abstract

በዓለም ላይ የሥነ ጽሑፍዘውጎችን የሚመረምሩ ጥናቶች እየተበራከቱ የመጡ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማዎችን ጉዳይ ይዘው የሚነሱቱ ግን ውስን ናቸው። እነዚህንና መሰል ክፍተቶች መነሻ በማድረግ፣ ይህ ጥናት ከእረኛዬ ድራማ የተገኙ ማህበረሰባዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ አካሄዶችን ይዳስሳል፡፡ ከአጠናን ዘዴ አኳያ ጥናቱ የተመሰረተው ፍጹም አይነታዊ (pure qualitative) በሆነ ውስን የጥናት ዘዴ ሲሆን የይዘታዊ ትንተና (content analysis) በመጠቀም በድራማው ውስጥ አሉ የተባሉ አበይት ጭብጦች ላይ ትኩረት ተደርጓል። በአራት ምዕራፎች ከተዋቀሩባቸው 48 የድራማው ክፍሎች ላይ 29 ክፍሎች ታላሚ የናሙና ስልት በመጠቀም ተመርጠዋል። የድራማው እምቅ ጭብጦች እና የተንጸባረቁባቸው መንገዶች በይዘታዊ ትንተና ስልት ተብራርተዋል። በዚህም መሠረት ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ሰባት የልማት አካሄዶች የተለዩ ሲሆን እነዚህም፡- የሀገር በቀል እውቀትን በልማት ማሳለጥ፣ ማህበረሰብን በትምህርት ማብቃት፣ ጎጂ ልማዶችን መዋጋት፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ ለአገራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት፣ ተተኪውን ትውልድ በመልካም ሥነምግባር ማብቃት፣ እና የሀገር ጠላቶችን እና አላማቸውን መለየት ናቸው። በመጨረሻም አገራት የዜጎቻቸውን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን፣ አገራዊ ጥቅምና ክብራቸውን ለማስጠበቅ እና እንደአገር መቀጠል ካለባቸው ከነዚህ የልማት አካሄዶች መማር መተኪያ ሌለው አማራጭ እንደሆነ ከድራማው ትምህርት ሊቀስሙ እንደሚገባ ጥናቱ ጠቁሟል። በመጨረሻም የጥናቱ አንድምታዎችና ሊሄድባቸው ያልቻላቸውን ጉዳዮች በመጠቆም፣ ተጨማሪ ጥናቶች ሊካሄዱ እንደሚገባ ፍላጎቱ ላላቸው ተመራማሪዎች ጥሪው ቀርቧል።

National Academic Digital Repository of Ethiopia
Openalex Percentile: Top 58%
Diverse Approaches in Healthcare and Education Studies
AI Navigator

Ask Laika to Summarize, Analyze, and Connect papers live on the map.

Summarize Papers & Methodologies

Extract key findings, datasets, and comparative methods across publications.

Benchmark Rankings & Visual Analytics

Rank top research institutions, authors, funders, topics, and journals by Field-Weighted Citation Impact (FWCI) and paper volume with instant charts.

Connect Distant Disciplines

Bridge topological clusters on the map to find hidden collaborative intersections.